Meskel Ethiopia

ሰበር ዜና – የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ More »

teddyafro

Teddy Afro chosen for World Cup 2014 Official African Singer

Teddy Afro chosen for World Cup 2014 Official Singer for Africa. Teddy Afro’s Song will be featured as the official song for the 2014 World Cup for Africa. ቴዲ አፍሮ ለታላቅ ዓለም More »

ቴዲ አፍሮ ሰጥቶታል በተባለው ቃለመጠይቅ ውዝግብ 10 ሚሊዮን ብር አጣ

enqu-magazines-cover-quoting-teddy-afro-as-saying-for-me-meniliks-unification-campaign-was-a-holy-war-ethiopia

(ሰንደቅ ጋዜጣ) ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በቅርቡ “የፍቅር ጉዞ” በሚል ለአንድ ዓመት የሚቆይ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ በደሌ ቢራ ፋብሪካን ከገዛው ሄኒከን ኩባንያ ጋር ውል ቢፈራረምም አፄ ሚኒሊክን በተመለከተ በዕንቁ መጽሔት ሰጥቶታል ከተባለው ቃለምልልስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ ሄኒከን ውል ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል። ቴዲ ለዚህ ኮንሰርት የተፈራረመውን ገንዘብ በይፋ ለመግለፅ ፈቃደኛ ባይሆንም፤ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘነው መረጃ መሠረት 10 ሚሊየን ብር እንደነበረ ታውቋል።

ቴዲ አፍሮ ከሄኒከን ጋር ቀደም ብሎ ገብቶት በነበረው ውል መሠረት ጥር 3 ቀን 2006 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ የኮንሰርት ዝግጅቱን የሚጀምር የነበረ ሲሆን በቀጣይም በአዳማ፣ በጅማ እና በአዲስ አበባ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ዓላማውም በፍቅር አንድነትን ለማምጣት የታሰበ እንደነበር በቅርቡ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መገለፁ አይዘነጋም።

ቴዲ አፍሮ ለዕንቁ መፅሔት አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያካሄዱት ጦርነት “ቅዱስ ጦርነት” ነው በሚል ቃለ ምልልስ ሰጥቷል ከተባለ በኋላ በተለይ እንደፌስቡክና ቲዊተር ባሉ ማኅበራዊ ድረገጾች በርካታ ወገኖች ተቃውሞ ከማስማት አልፈው ፒቲሽን በመፈራረም ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። ቴዲ አፍሮ ቃለምልልሱን እንዳላደረገ ቢያስተባብልም ሁኔታው ከመርገብ ይልቅ ተባብሶ “በደሌ ቢራን አትጠጡ” የሚል ዘመቻ ሊከፈት ችሏል።

ጉዳዩ ያሳሰበው ሄኒከን ኩባንያ ከቴዲ ጋር የገባውን ውል ለማፍረስ መገደዱ የታወቀ ሲሆን፤ የሄኒከን ውሣኔ በማኅበራዊ ድረገጾች ከተከፈተው ዘመቻ ጋር በቀጥታ ይያያዝ፣ አይያያዝ ግን ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።Residents make way for new stadium

The New Addis Ababa Stadium Design

The area between Bole Medhanialem and Imperial Hotel is being cleared to make way for the construction of a 60,000-seat stadium, estimated to cost 1.6 billion birr. Residents of the area, commonly known as “Chereqa sefer, have been relocated, as many houses had to be demolished for the construction. Many squatters have also been removed from the area.
Last year in June the Federal Sport Commission officially declared the winner of the new architectural design of the new stadium that it plans to build. The Winner of the design was reportedly JDAW and its engineers.
The stadium will be Ethiopia’s first that is up to FIFA’s standards and guidelines. Currently there are only two stadiums in Addis Ababa. The Addis Ababa Stadium which was built by Emperor Haile Selassie half a century ago. Another stadium, which has yet to be fully finished, is Abebe Bikila Stadium.
It was reported that the commission believes the old stadiums are preventing them from holding more football matches. In addition, the bigger stadium will generate more revenue, as is common for other nearby countries that have bigger stadiums.ወጣቱን በብረት ቀጥቅጠው ገድለዋል የተባሉ ተያዙ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ነዳጅ ለመቅዳት ወደ “ኦይል ሊቢያ” የሄደውን የ24 አመት ወጣት ሙባረክ ሱልጣንን በብረት ቀጥቅጠው ገድለዋል በሚል የተጠረጠሩ አምስት የነዳጅ ማደያው ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ሟች ወጣት ሙባረክ፤ ታህሳስ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ከመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ወዳለው “ኦይል ሊቢያ” የሄደው የመኪናው ነዳጅ አልቆበት በጀሪካን ለመቅዳት ነበር፡፡ “ቤንዚን በጀሪካን አንቀዳም፣ በሊትር ነው” በሚል በተነሳ ውዝግብ፣ ከነዳጅ ቀጂዎቹ ጋር ጠብ ውስጥ መግባቱን የተናገሩት ቤተሰቦቹ፤ የነዳጅ ማደያው ሰራተኞች ልጃቸውን በብረት ጭንቅላቱና ጀርባው ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደደበደቡትና ታናሽ ወንድሙ ሊገላግል ሲገባም በያዙት ብረት እሱንም ደብድበው ጉዳት እንደደረሱበት ገልፀዋል፡፡
በድብደባው ክፉኛ የተጐዳውን ልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መውሰዳቸውን የጠቆሙት ቤተሰቦች፤ “ከአቅማችን በላይ ነው” የሚል ምላሽ ከሆስፒታሉ በማግኘታቸው፣ ወደ ኮሪያ ሆስፒታል ወስደው እንዳስተኙትና ለሁለት ቀን ህክምና ሲደረግለት ከቆየ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ ተናግረዋል፡፡
ሟቹ ወጣት፤ ሰው አክባሪና ታታሪ ሰራተኛ እንደነበር ያስታወሱት ቤተሰቦቹ፤ በመልካም ባህሪው ከሠው ጋር ተግባብቶ ከመስራት ውጪ ከማንም ጋር ተጣልቶ እንደማያውቅ መስክረዋል፡፡ በድብደባው ወቅት በኪሱ ይዞት የነበረው ገንዘብና ሞባይሉ መሰረቁን ገልፀው፤ ልጃቸው በገዛ ሀገሩ ላይ በብረት ተቀጥቅጦ መገደሉ ክፉኛ እንዳሳዘናቸው በሃዘን ተሞልተው ተናግረዋል፡፡
ጉለሌ ወደሚገኘው “ኦይል ሊቢያ” ሄደን ነገሩን ለማጣራት ብንሞክርም፤ ባለቤቱን ጨምሮ የማደያው ሰራተኞች በፖሊስ ስለተወሰዱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አልቻልንም፡፡ ፖሊስ ከግድያው ጋር በተያያዘ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያኮሄደ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡Bedele Brewery cancels Teddy Afro’s “Journey of Love” Concert

tedy-afro-yefikir-guzo-concert

Awramba Times (Addis Ababa) – Confidential sources close to Awramba Times disclosed that Bedele brewery, Heineken NV’s subsidiary in Ethiopia has cancelled Teddy Afro’s nationwide “Journey of Love” Concert.

Oromo Activists called on Bedele brewery to stop sponsoring Tewodros Kassahun’s nationwide tour that was scheduled across different cities of Ethiopia?

Two weeks ago, Ethiopian singer Tewodros Kassahun (aka Teddy Afro) told the local Enqu magazine that he considered emperor Minelik’s imperial expansion a “holy war”. This remark deeply offended thousands of Oromos as an ethnically-motivated “remark” against Ethiopia’s largest ethnic group.

Oromo activists all over the world had campaigned beer drinkers in Ethiopia to ditch Bedele products and also pressure regional officers to withdraw the sponsorship.Eritrean pilot who bombarded Makalle’s Aider school defects to Djibouti

eritrean-Air-Force1-300x225

Habtom Kahsay, an Eritrean Air Force pilot has escaped with his bomber in Djibouti and plans seeking political asylum in another country. According to data collected by the Africa Express, the same pilot who in 1998 at the outbreak of war with Ethiopia stood up in flight from Asmara and bombarded Aider elementary school in Makalle, Tigray.

2013 was a year of leaks of military pilots from the former Italian colony, ruled by a harsh dictatorship is at least 10 officers who have fled, many of them in Saudi Arabia. In early December, although the national football team of Eritrea, who was engaged in an international tournament in Nairobi, has requested political asylum and has not returned home.

Source: Africa ExPressNew Ethiopian dam won’t affect Egypt’s water supply: minister

Gonder Egypt minister

Minister Mohamed Abdel Moteleb says a new dam in Gondar will not affect water flow to Lake Nasser
The construction of a new dam in Ethiopia will not affect the supply of water flowing to Egypt, said Egyptian Minister of Irrigation and Water Resources on Saturday.

Construction on the Megech Dam, located near the Ethiopian city of Gondar, began earlier this month and has been allocated funding of approximately USD $125m, according to privately-owned Ethiopian Walta and its Information and Public Relations Center. The dam is planned to hold 1.
8 billion cubic metres of water when it is constructed, and will be used for irrigation purposes and drinking water for Gondar.

The effects of the dam have already been studied, said Egyptian minister Mohamed Abdel Moteleb, and have been presented by the Ethiopian government as part of one of the projects included in the eastern Nile Basin Initiative, an initiative that all Nile Basin countries have agreed upon.ዕንቁ መፅሔት ቆርጦ አስቀርቶታል የተባለው የቴዲ አፍሮ አስተያየት

enqu-magazines-cover-quoting-teddy-afro-as-saying-for-me-meniliks-unification-campaign-was-a-holy-war-ethiopia

(Daniel Berhane)

ዕንቁ፡- ዳግማዊ ምኒልክ ስለዛሬይቱ ኢትዮጵያ መፈጠር ሲሉ የገቡበትን ጦርነት እንዴት ነው የምትመለከተው?

ቴዎድሮስ፡- ምኒልክ በዚያን ጊዜ ያካሄዷቸው ፖለቲካዊ ተግባራት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች በመዘዋወር ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የገቡበት ጦርነት ለእኔ ቅዱስ ጦርነት ነው። ይህም የራሴ ዕምነት ነው። ምንጊዜም ሰዎች የሚበጃቸውን ነገር እስኪገነዘቡት ድረስ ያለመግባባቱ መጠን ይሰፋል። ያም ግጭት ሊፈጥር ይችላል። ወይም ደግሞ በእኛ ሀገር ሁኔታ ብቻ የተከሰተ ሳይሆን በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሆነም ነው። እንዲህም ሆኖ ግን ምኒልክ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ዘምተው ንጉሥ ጦናን ማርኩ። ከማረኳቸውም በኋላ እግራቸውን እያጠቡ ‹‹የእኛ አንድ አለመሆን፣ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት አለመመሥረታችን፤ የጋራ ለሚሆነው ጠላታችን ጥቃት አሳልፎ የሚሰጠን አደገኛ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። በዚህ ምክንያት ነው ወደ አንተ ጦር ያዘመትኩት እንጂ ሥልጣንህን ለመቀማትና በአንተ ላይ ለመግነን… ፈልጌ አይደለም። ማእከላዊ መንግሥታችንን ማጠናከሩ ግን ሁላችንንም የሚጠቅመን ነው። አገራችንን፣ በሕላችንን፣ ታሪካችንን፣ ቋንቋችንን ጠብቀንና ድንበራችንን አስከብረን ለመኖር ይረዳናል›› ነበር ያሏቸው።

እንግዲህ ምኒልክ ንጉሥ ጦናን አሏቸው እንደሚባለውም ይሁን በሌሎችም ብሔራዊ ክብርንና ማንነትን አስጠብቆ ለመኖር በሚያስችለው ፖለቲካዊ መመዘኛ ሲታይ፤ ቋንቋንም ጠብቆ ለመኖር እንኳ ቢያስፈልግ… ከጠላት ማንኛውም ጥቃት ራስን መከላከል ወይም ማስከበር በሚቻልበት አቅም መጠን መኖርን የግድ ይላል። ምናልባትም በዚያን ጊዜ እንደ ምኒልክ ያለው ባለውለታ ተፈጥሮልን… ከጠላት ተጠብቀን መኖር ባንችል ኖሮ፤ ዛሬ የምንጠራበት ስማችን ኢትዮጵያዊ ቀለም ሊኖረው አይችልም ነበር። እኔም ቴዎድሮስ፣ ሌላውም ምኒልክ፣ ጥላሁን፣ ፀሐይ… አንባልም ነበር። የነበረው ቋንቋችን ሁሉ ይጠፋ ነበር። ግን ቋንቋንም፣ ባሕልንም ሰብስቦ ለመያዝ፤ ከዛም በላይ ደግሞ ሕዝብን አስተባብሮ በአንድነት ለመሥራት፤ የአንድነትን ታላቅ ዋጋ ቀድሞ መገንዘብ ያስፈልጋል። ያንን ቅዱስ ያልኩትን ጦርነት ሊያስነሳው የቻለውም ይኸው ግንዛቤ ይመስለኛል።የ5 ዓመት ህፃን ከት/ቤት ፎቅ ወድቃ ሞተች

አራት የት/ቤቱ ሰራተኞች ከስራ ታግደዋል

(አዲስ አድማስ)የምሥራቅ ጮራ መዋለ ህፃናትና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የመዋዕለ ህፃናት ተማሪ የነበረችው የ5 ዓመቷ ህፃን ሳባህ አማን ከት/ቤቱ 3ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ በአራተኛ ቀኗ ባለፈው እሁድ ህይወቷ አልፏል፡፡ ጉሊት በመነገድ ከሚተዳደሩ አክስቷና ከ12ኛ ክፍል ተማሪ እህቷ ጋር ትኖር የነበረችው ሕፃን በአሁኑ ዓመት ነበር ትምህርት ቤት የገባችው፡፡ ለብቻው ከተከለለው መዋዕለ ህፃናት እንዴት ወደ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታ፣ ከፎቅ ላይ እንደወደቀች እንደማያውቁ የተናገሩት ቤተሰቦች፤ ህፃኗን ስትወድቅ ማንም እንዳልነበረና የትምህርት ቤቱ የካፍቴሪያ ሰራተኛ መሬት ላይ ወድቃ እንዳገኛት ጠቁመዋል፡፡ ልጅቷ ስትወድቅ እንዴት አስተማሪዎች ወይም ሞግዚቶች እንዳላዩ ት/ቤቱን መጠየቃቸውን የገለፁት ቤተሰቦች፤ ከት/ቤቱ “ስብስባ ላይ ነበርን” የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ የምስራቅ ጮራ ት/ቤት ርእሰ መምሕር አቶ ስንታየሁ አንሺሱ ስለ አደጋው ሲናገሩ፤ “ሳምንታዊ ስብሰባ የምናደርግበት ቀን ስለነበር አጠቃላይ የት/ቤቱ መምህራንና ሰራተኞች ተሰብስበን ሳለ ከቀኑ 9፡40 ላይ አንዲት ተማሪ ከፎቅ ወድቃለች ተባልን።

ወዲያው ህፃኗን አንስተን ወደ ምግባረ ሰናይ ሆስፒታል ወሰድናትና ወደ ጥቁር አንበሳ ላኩን። እዚያም ከፍለን አሳከምናት” ብለዋል፡፡ ሆኖም ህፃኗ በወደቀች አራተኛ ቀኗ ህይወቷ አልፏል፡፡ ህፃኗ እንዴት ትምህርት ቤት ውስጥ ለብቻዋ እንደቀረች የተጠየቁት ርዕሰ መምህሩ፤ ብቻውን እንዳልነበረችና 5 ህፃናት አብረዋት እንደነበሩ ተናግረዋል፡፡ ህፃናቱን ለብቻቸው ትተው ስብሰባ መግባታቸው አግባብ ነው ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ስንታየሁ፤ ወላጆች ልጆቻቸውን በጊዜ እንዲወስዱ ማስታወቂያ መለጠፋቸውንና በቃልም መንገራቸውን ገልፀዋል፡፡ በህፃኗ ላይ ለደረሰው የሞት አደጋ ተጠቂው ማን እንደሆነና የተወሰደ እርምጃ ስለመኖሩ የተጠየቁት የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር፤ “ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አራት ሰራተኞች ከስራ አግደናል፤ ሁለት ሞግዚቶችና ሁለት ጥበቃዎች ደግሞ ጉዳያቸው በዲሲፕሊን ኮሚቴ እየተጣራ ነው” ብለዋል፡፡