Limalimo-Lodge-Logo-168x150

U.S. $1 Million Limalimo Lodge to open in 2015 at Simien Mountains

Addis Ababa ,July 15/2014, African Wildlife Capital, a mission-based investment company has signed agreements with a British-Ethiopian venture to build a world-class boutique hotel in Ethiopia’s Simien Mountains National Park, one of More »

Meskel Ethiopia

ሰበር ዜና – የመስቀል ክብረ በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

የኢትዮጵያው የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ዩኔስኮ አስታወቀ፡፡ ዩኔስኮ የመስቀል ክብረ በዓልን (Commemoration feast of the finding of the True Holy Cross of Christ) በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን ኅዳር 25 ቀን ይፋ More »

South Sudan talks resume in Addis Ababa nightclub Gaslight (BBC)

_72251660_ziox36qh

(BBC)A shift in the venue for talks aimed at brokering a ceasefire in South Sudan has left some delegates bemused.

The government and rebel teams have moved to the dance floor of a top nightclub in an Addis Ababa hotel.

The Gaslight club was selected after the room in the Sheraton hotel the teams had been using was booked by a Japanese delegation.

Sources close to the talks said some delegates were unhappy with the poor lighting and excess noise.

Daytime talks

Talks aimed at securing the ceasefire in the month-long conflict in South Sudan have now resumed in the Ethiopian capital.

But the delegates are now in the basement of the luxury hotel, amid faux gold columns.

South African preacher makes congregation eat GRASS to ‘be closer to God’ ደቡብ አፍሪካዊው ሰባኪ ተከታዮቹ ሣር እንዲበሉ አዘዘ

safe_image.php

A South African preacher made his congregation eat grass to ‘be closer to God’ before stamping on them.

Under the instruction of Pastor Lesego Daniel of Rabboni Centre Ministries dozens of followers dropped to the floor to eat the grass at his ministry in Garankuwa, north of Pretoria after being told it will ‘bring them closer to God.’

His controversial methods have drawn criticism from thousands of people although members of his congregation swear by his methods – he is said to have claimed that humans can eat anything to feed their bodies and survive on whatever they choose to eat.

A South African preacher made his congregation eat grass to 'be closer to God' before stamping on themA South African preacher made his congregation eat grass to ‘be closer to God’ before stamping on them

የመንግስት ሠራተኛው በመንግስት ላይ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አነሳ

cbc0a2198d8b19383435ab41ab4960fc_L

“ኬኩ አላደገም” አቶ ሶፊያን አህመድ

(ሰንደቅ ጋዜጣ) ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ በመንግስትና በመንግስት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም በግል ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞችን የሚወክሉ ከልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች የተውጣጡ የሰራተኛ ማህበራት ወኪሎች በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ባለመቻሉ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አቀረቡ።

በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን የሰራተኛው ጥያቄ በመሰረታዊነት ለመመለስ የሚቻለው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት (ኬኩ) ሲያድግ ነው የሚል ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የደመወዝ ገቢ ግብር ማሻሻያ እንደሚደረግ ግን ፍንጭ ተሰጥቷል።

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እስከ ስምንት ሰዓት በተካሄደው ውይይት ላይ የሰራተኞቹ ተወካዮች በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በአሁኑ ወቅት በሰራተኛው የተጫነው የኑሮ ውድነት ከእነቤተሰቡ ለረሀብ እንዲጋለጥ እያደረገው መሆኑን ገልጸዋል። ሰራተኛው አሁን በሚከፈለው ደመወዝ እየኖረ አይደለም። በምርታማነትም ላይ ከፍተኛ አደጋ በማንዣበቡ ከአቅሙ በላይ መሆኑ በስፋት ተነስቷል። በመሆኑም ከደመወዝ ጭማሪ ባሻገር የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲሻሻልና ሌሎች የማኅበራዊ ድጎማዎች እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።

በአሁኑ ወቅት በንግድ ድርጅቶች ተጥሎ የነበረው 45 ፐርሰንት የገቢ ታክስ ወደ 30 ፐርሰንት ዝቅ ቢልም በሰራተኛው ላይ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ 35 በመሆኑ ወደ 30 ፐርሰንት ዝቅ እንዲልና የዝቅተኛው የደመወዝ እርከን ላይ የተጣለውም የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲስተካከል ሲሉ ጠይቀዋል።

Ethiopia’s claims about dam construction ‘media show’: Egypt official

2014-635248121136821187-682

(Ahram Online) The Egyptian government has “alternative routes” in dealing with a major hydroelectric dam being constructed in Ethiopia, a spokesman for the Egyptian irrigation ministry said on Wednesday following a recent meeting between Egypt, Ethiopia and Sudan that was deemed a deadlock.

Spokesman Khaled Waseef said, in a press statement reported by MENA, that the Ethiopian Grand Renaissance Dam faces financial as well as technical problems, and that the Ethiopian government’s statements that the project has been 30 percent completed are a “media show” for its own political gains.

Waseef added that the construction levels of the dam are “extremely low” and that the project’s generator has “not even one brick [in place].”

He stated that the negotiations with Ethiopia will not resume until Ethiopia changes its position and “applies international standards” while constructing the dam. He said there are imminent dangers for Egypt if the dam continued to be built as planned, which is something “Egypt would never accept.”

‹‹ለዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሳካት የሚረዱ ሦስት የውጭ ኩባንያዎች የጠላት ሰለባ ሊሆኑ ነበር›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

cbc0a2198d8b19383435ab41ab4960fc_L

(ሪፖርተር) የአገሪቱን የዕድገትና ትራንስፌርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብለው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተመርጠው የገቡ ሦስት የውጭ ኩባንያዎች ላይ፣ ‹‹ጠላት ጥፋት ሊፈጽምባቸው እንደነበር ደርሰንበታል፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

‹‹ጠላት›› በተባለው አደጋ ሊደርስባቸው ነበር የተባሉት ሦስቱ የውጭ ኩባንያዎች የቱርኩ አይካ አዲስ፣ የሆላንዱ ሼር ኢትዮጵያና የቻይናው ሁንጂያን የጫማ አምራች ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ‹‹የጠላት የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ነበር፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም ይህንን የጥቃት ጉዳይ ያነሱት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ለመብታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ኢንዱስትሪዎችንም ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት እንዳለባቸውና አንዳንድ ሠራተኞችም በእኩይ ተግባር ላይ ሊሰማሩ እንደሚችሉ በመጠቆም ነው፡፡

ጥቃት ሊፈጸምባቸው ነበር ስላሉዋቸው ኩባንያዎች ጉዳይ ሲገልጹም፣ ‹‹እነዚህ ሦስት ኩባንያዎችን በአንድ ሳምንት በተመሳሳይ ቀን የገጠማቸውን ልንገራችሁ፡፡ የዕድገታችን ጠላት ይህንን መንግሥት ማሽመድመድ የሚቻለው እነዚህን ሦስት ድርጅቶች በመምታት ነው ብሎ አቅዶ በድርጅቶቹ ውስጥ በመሠረተው ሴል አማካይነት ለአንድ ቀን እንዲጨናነቁ አድርጓል፤›› ብለዋል፡፡

ቴዲ አፍሮ ሰጥቶታል በተባለው ቃለመጠይቅ ውዝግብ 10 ሚሊዮን ብር አጣ

enqu-magazines-cover-quoting-teddy-afro-as-saying-for-me-meniliks-unification-campaign-was-a-holy-war-ethiopia

(ሰንደቅ ጋዜጣ) ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በቅርቡ “የፍቅር ጉዞ” በሚል ለአንድ ዓመት የሚቆይ የሙዚቃ ኮንሰርት ለማቅረብ በደሌ ቢራ ፋብሪካን ከገዛው ሄኒከን ኩባንያ ጋር ውል ቢፈራረምም አፄ ሚኒሊክን በተመለከተ በዕንቁ መጽሔት ሰጥቶታል ከተባለው ቃለምልልስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብ ሄኒከን ውል ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል። ቴዲ ለዚህ ኮንሰርት የተፈራረመውን ገንዘብ በይፋ ለመግለፅ ፈቃደኛ ባይሆንም፤ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ባገኘነው መረጃ መሠረት 10 ሚሊየን ብር እንደነበረ ታውቋል።

ቴዲ አፍሮ ከሄኒከን ጋር ቀደም ብሎ ገብቶት በነበረው ውል መሠረት ጥር 3 ቀን 2006 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ የኮንሰርት ዝግጅቱን የሚጀምር የነበረ ሲሆን በቀጣይም በአዳማ፣ በጅማ እና በአዲስ አበባ ለማካሄድ ታቅዶ ነበር። ዓላማውም በፍቅር አንድነትን ለማምጣት የታሰበ እንደነበር በቅርቡ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መገለፁ አይዘነጋም።

ቴዲ አፍሮ ለዕንቁ መፅሔት አፄ ሚኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያካሄዱት ጦርነት “ቅዱስ ጦርነት” ነው በሚል ቃለ ምልልስ ሰጥቷል ከተባለ በኋላ በተለይ እንደፌስቡክና ቲዊተር ባሉ ማኅበራዊ ድረገጾች በርካታ ወገኖች ተቃውሞ ከማስማት አልፈው ፒቲሽን በመፈራረም ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። ቴዲ አፍሮ ቃለምልልሱን እንዳላደረገ ቢያስተባብልም ሁኔታው ከመርገብ ይልቅ ተባብሶ “በደሌ ቢራን አትጠጡ” የሚል ዘመቻ ሊከፈት ችሏል።

ጉዳዩ ያሳሰበው ሄኒከን ኩባንያ ከቴዲ ጋር የገባውን ውል ለማፍረስ መገደዱ የታወቀ ሲሆን፤ የሄኒከን ውሣኔ በማኅበራዊ ድረገጾች ከተከፈተው ዘመቻ ጋር በቀጥታ ይያያዝ፣ አይያያዝ ግን ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

Residents make way for new stadium

The New Addis Ababa Stadium Design

The area between Bole Medhanialem and Imperial Hotel is being cleared to make way for the construction of a 60,000-seat stadium, estimated to cost 1.6 billion birr. Residents of the area, commonly known as “Chereqa sefer, have been relocated, as many houses had to be demolished for the construction. Many squatters have also been removed from the area.
Last year in June the Federal Sport Commission officially declared the winner of the new architectural design of the new stadium that it plans to build. The Winner of the design was reportedly JDAW and its engineers.
The stadium will be Ethiopia’s first that is up to FIFA’s standards and guidelines. Currently there are only two stadiums in Addis Ababa. The Addis Ababa Stadium which was built by Emperor Haile Selassie half a century ago. Another stadium, which has yet to be fully finished, is Abebe Bikila Stadium.
It was reported that the commission believes the old stadiums are preventing them from holding more football matches. In addition, the bigger stadium will generate more revenue, as is common for other nearby countries that have bigger stadiums.

ወጣቱን በብረት ቀጥቅጠው ገድለዋል የተባሉ ተያዙ

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ነዳጅ ለመቅዳት ወደ “ኦይል ሊቢያ” የሄደውን የ24 አመት ወጣት ሙባረክ ሱልጣንን በብረት ቀጥቅጠው ገድለዋል በሚል የተጠረጠሩ አምስት የነዳጅ ማደያው ሠራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ሟች ወጣት ሙባረክ፤ ታህሳስ 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ከመኖሪያ ቤቱ አቅራቢያ፣ ጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ወዳለው “ኦይል ሊቢያ” የሄደው የመኪናው ነዳጅ አልቆበት በጀሪካን ለመቅዳት ነበር፡፡ “ቤንዚን በጀሪካን አንቀዳም፣ በሊትር ነው” በሚል በተነሳ ውዝግብ፣ ከነዳጅ ቀጂዎቹ ጋር ጠብ ውስጥ መግባቱን የተናገሩት ቤተሰቦቹ፤ የነዳጅ ማደያው ሰራተኞች ልጃቸውን በብረት ጭንቅላቱና ጀርባው ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደደበደቡትና ታናሽ ወንድሙ ሊገላግል ሲገባም በያዙት ብረት እሱንም ደብድበው ጉዳት እንደደረሱበት ገልፀዋል፡፡
በድብደባው ክፉኛ የተጐዳውን ልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መውሰዳቸውን የጠቆሙት ቤተሰቦች፤ “ከአቅማችን በላይ ነው” የሚል ምላሽ ከሆስፒታሉ በማግኘታቸው፣ ወደ ኮሪያ ሆስፒታል ወስደው እንዳስተኙትና ለሁለት ቀን ህክምና ሲደረግለት ከቆየ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ ተናግረዋል፡፡
ሟቹ ወጣት፤ ሰው አክባሪና ታታሪ ሰራተኛ እንደነበር ያስታወሱት ቤተሰቦቹ፤ በመልካም ባህሪው ከሠው ጋር ተግባብቶ ከመስራት ውጪ ከማንም ጋር ተጣልቶ እንደማያውቅ መስክረዋል፡፡ በድብደባው ወቅት በኪሱ ይዞት የነበረው ገንዘብና ሞባይሉ መሰረቁን ገልፀው፤ ልጃቸው በገዛ ሀገሩ ላይ በብረት ተቀጥቅጦ መገደሉ ክፉኛ እንዳሳዘናቸው በሃዘን ተሞልተው ተናግረዋል፡፡
ጉለሌ ወደሚገኘው “ኦይል ሊቢያ” ሄደን ነገሩን ለማጣራት ብንሞክርም፤ ባለቤቱን ጨምሮ የማደያው ሰራተኞች በፖሊስ ስለተወሰዱ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አልቻልንም፡፡ ፖሊስ ከግድያው ጋር በተያያዘ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያኮሄደ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡