Category Archives: Politics

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ

ALEMYEHU ATOMSSA

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድርና የኦህዴድ የቀድሞው ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው ነው ዛሬ ለሊት ሰባት ሰዓት ላይ ያረፉት።

አቶ አለማየሁ ከየካቲት 9 ቀን 2006 ጀምሮ በባንኮክ ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደቆዩ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው።

በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው አቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም ነው የተወለዱት አቶ አለማየሁ።

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫም ፥ ላለፉት 24 ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እና መላው የአገሪቱ ህዝቦች ዛሬ ለደረሱበት የሰላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ተጠቃሚነት እንዲበቁ በቁርጠኝነት የታገሉ ነባር ታጋይ ነበሩ ብሏል።

በ1981 ዓመተ ምህረት የደርግን ስርዓት ለመገርሰስ ሲካሄድ የነበረውን የትጥቅ ትግል ተቀላቅለዋል።

ከ1988 እስከ 1994 ድረስም የኦህዴድ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት እና የድርጅቱ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ በመሆን አገልግለዋል።

ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የኦህዴድ ሊቀመንበር ሆነው ፥ ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ደግሞ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ሰርተዋል።

የአቶ አለማየሁ አስክሬን ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ፥ የቀብር ስነስርዓታቸውን የሚያስፈፀም ኮሚቴም በመንግስት ተቋቁማል።ለሕዝብ ግልፅ ያልሆነው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ

Polticazed

በቅርቡ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኀሳቦች እየተነሱ ነው። በተለይ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካርቱምን ከጎበኙ በኋላ ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ የድንበሩ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።

የካርቱም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የድንበር ማካለል አለመግባባት (Demarcation disputes) በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ዘግበዋል። የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ ከርቲ ሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል ችግራቸውን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሱዳኖቹ “ፍሻጋ” በማለት በሚጠሩት አካባቢ ያለው የድንበር ችግር ይፈታል ብለው እንደሚያስቡ እየገለፁ ነው። በሌላ ወገን በርካታ ኢትዮጵያውያን መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሁለቱም አገሮች ሰላማዊ የድንበር ቀጠና እንዲኖራቸው እየሰሩ ነው ከማለታቸው ባለፈ፤ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በቀጣይም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ይገልፃሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይሄው ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመሳቡ በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የማካለል ስራው እንደሚከናወን መግለፃቸው አይዘነጋም። ይኼው የድንበር ማካለል ከጥቂት ወራት በኋላ ሊከናወን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ነገር ግን የማካለል ሂደቱ በምን መልኩ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።

በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ግን የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ በመንግስት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አረናም ሆነ አንድነት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።Leaked tape From Abebe Gelaw Presented by Kebede Kassa

index

Editor’s note: የተቃዋሚ አክቲቪስት የሆነው አበበ ገላው በግንቦት 2004 የቀድሞው ጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የተገኙበት ስብሰባ ላይ የተቃውሞ ጩኸት ካሰማ ከወራት በኋላ፤ ከግንቦት ሰባት ድርጅት መሪ ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የበለጠ ትኩረት ስቧል በሚል ከኢሳት ገለል እንዲል ተደርጎ በነበረበት ወራት በግል ያደረጋውን ንግግር የድምጽ ቅጂ፤ HornAffairs ከታማኝ ምንጮች አግኝቷል፡፡
የአበበ ገላውን ኑዛዜ የHornAffairs ብሎገር የሆነው ከበደ ካሣ እንደሚከተለው አቅርቦታል፡፡
**************

(ከበደ ካሣ)

ይህን የ11 ደቂቃ የተቀረፀ ድምፅ ጋብዣችኋለሁ፡፡ ከየት አመጣኸው እንዳትሉኝ፡፡ ዊክ ሊክስ ወይም ስኖውደን ብቻ ናቸው እንዴ አፈትልኮ የወጣ መረጃ የሚያሰረጩት? በመረጃው ትክክለኛነት ላይ ተማምናችሁ ዝም ብላችሁ ኮምኩሙት፡፡

እንደኔ እንደኔ ሙሉውን ቅጂ ብታዳምጡት መልካም ነው፡፡ በደካማ ኢንተርኔትና በጊዜ ማጣት የተነሳ ሙሉውን ማድመጥ ካልቻላችሁ ግን ሙሉ መረጃው በዚህ ፅሁፍ ቀርቦላችኋል፡፡ ልዩነቱ ይሄኛው በፅሁፍ ሲሆን ያኛው በድምፅ መቅረቡ ነው፡፡ ታዲያ ልክ እንደ አበበ ገላው እዚህም እዚያም መዝለል እንዳይሆንባችሁ ታዲያ ሙሉ ንግግሩ በሶስት አበይት ርዕሶች ተደራጅቶላችኋል፡፡ ሲያስፈልግ ደግሞ ንግግሩ እንደወረደ በጥቅስ ምልክት ውስጥ ተቀምጧል፡፡

በርግጥ ያመንከው ሰው ሲከዳህ ወይም የተማመንክበት ሰው ከንቱ መሆኑ ሲነገርህ ሁኔታውን መርምረህ እውነቱን ከመቀበል ይልቅ የወዳጅህን ጉድ ያጋለጠብህን ሰው ማጥላላት የማህበራዊ ድረ-ገፆቻችን መገለጫ ከሆነ ሰንብቷል፡፡ እና ቢሆንም እንዲህ አይነት አመል ያላችሁ ቢያንስ ለዚች ጉዳይ ብቻ አደብ ገዝታችሁ እንድታመዛዝኑ እጠይቃችኋለሁ፡፡

1. አበበ ገላውና የተቃውሞው ጎራ

በሀገር ውስጥ ባለው የተቃዋሚ ጎራ መካከል የይስሙላ ካልሆነ በቀር የአላማ አንድነት እንደሌለ በተደጋጋሚ በተፈፀሙ ድርጊቶች ተጋልጧል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውህደት ድርድር የሚያሳልፉትን ጊዜ ያክል በፍቺ ድርድር ላይም ያሳልፋሉ፡፡ ከመዋሃዳቸው በፊት ርስ በርስ የሚደናነቁትን ያክል ርስ በርስ ለመነቃቀፍም ፋታ አይወስድባቸውም፡፡ እድሜውን አንዱን በመቀበልና ሌላውን በመሸኘት እየገፋ ያለው ‹‹መድረክ›› (በረጅሙ – ‹‹የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ››) ለዚህ ህያው አብነት ነው፡፡ ተጨማሪ ዐብነት ካስፈለገ የ1997ቱን ቅንጅትን መመረቅ ይቻላል፡፡ በዚህ በኩል የማይታማው ሰማያዊ ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ እድሜው አጭር ቢሆንም ራሱን ተራራ አሳክሎ ሌሎቹን በንቀት ቁልቁል ስለሚያያቸው በቀላሉ የሚዋሃዱት አይሆንም፡፡ እንትፍ ትፍ፤ ከአይን ያውጣህ ብያለሁ፡፡South Sudan talks resume in Addis Ababa nightclub Gaslight (BBC)

_72251660_ziox36qh

(BBC)A shift in the venue for talks aimed at brokering a ceasefire in South Sudan has left some delegates bemused.

The government and rebel teams have moved to the dance floor of a top nightclub in an Addis Ababa hotel.

The Gaslight club was selected after the room in the Sheraton hotel the teams had been using was booked by a Japanese delegation.

Sources close to the talks said some delegates were unhappy with the poor lighting and excess noise.

Daytime talks

Talks aimed at securing the ceasefire in the month-long conflict in South Sudan have now resumed in the Ethiopian capital.

But the delegates are now in the basement of the luxury hotel, amid faux gold columns.የመንግስት ሠራተኛው በመንግስት ላይ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አነሳ

cbc0a2198d8b19383435ab41ab4960fc_L

“ኬኩ አላደገም” አቶ ሶፊያን አህመድ

(ሰንደቅ ጋዜጣ) ቅዳሜ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ በመንግስትና በመንግስት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም በግል ተቋማት የሚሰሩ ሰራተኞችን የሚወክሉ ከልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች የተውጣጡ የሰራተኛ ማህበራት ወኪሎች በአሁኑ ወቅት ያለውን የኑሮ ውድነት መቋቋም ባለመቻሉ የኑሮ ውድነት ማሻሻያ ድጎማ ጥያቄ አቀረቡ።

በዕለቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን የሰራተኛው ጥያቄ በመሰረታዊነት ለመመለስ የሚቻለው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት (ኬኩ) ሲያድግ ነው የሚል ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የደመወዝ ገቢ ግብር ማሻሻያ እንደሚደረግ ግን ፍንጭ ተሰጥቷል።

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተኩል እስከ ስምንት ሰዓት በተካሄደው ውይይት ላይ የሰራተኞቹ ተወካዮች በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በአሁኑ ወቅት በሰራተኛው የተጫነው የኑሮ ውድነት ከእነቤተሰቡ ለረሀብ እንዲጋለጥ እያደረገው መሆኑን ገልጸዋል። ሰራተኛው አሁን በሚከፈለው ደመወዝ እየኖረ አይደለም። በምርታማነትም ላይ ከፍተኛ አደጋ በማንዣበቡ ከአቅሙ በላይ መሆኑ በስፋት ተነስቷል። በመሆኑም ከደመወዝ ጭማሪ ባሻገር የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲሻሻልና ሌሎች የማኅበራዊ ድጎማዎች እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል።

በአሁኑ ወቅት በንግድ ድርጅቶች ተጥሎ የነበረው 45 ፐርሰንት የገቢ ታክስ ወደ 30 ፐርሰንት ዝቅ ቢልም በሰራተኛው ላይ ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ 35 በመሆኑ ወደ 30 ፐርሰንት ዝቅ እንዲልና የዝቅተኛው የደመወዝ እርከን ላይ የተጣለውም የደመወዝ ገቢ ግብር እንዲስተካከል ሲሉ ጠይቀዋል።Ethiopia’s claims about dam construction ‘media show’: Egypt official

2014-635248121136821187-682

(Ahram Online) The Egyptian government has “alternative routes” in dealing with a major hydroelectric dam being constructed in Ethiopia, a spokesman for the Egyptian irrigation ministry said on Wednesday following a recent meeting between Egypt, Ethiopia and Sudan that was deemed a deadlock.

Spokesman Khaled Waseef said, in a press statement reported by MENA, that the Ethiopian Grand Renaissance Dam faces financial as well as technical problems, and that the Ethiopian government’s statements that the project has been 30 percent completed are a “media show” for its own political gains.

Waseef added that the construction levels of the dam are “extremely low” and that the project’s generator has “not even one brick [in place].”

He stated that the negotiations with Ethiopia will not resume until Ethiopia changes its position and “applies international standards” while constructing the dam. He said there are imminent dangers for Egypt if the dam continued to be built as planned, which is something “Egypt would never accept.”‹‹ለዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሳካት የሚረዱ ሦስት የውጭ ኩባንያዎች የጠላት ሰለባ ሊሆኑ ነበር›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

cbc0a2198d8b19383435ab41ab4960fc_L

(ሪፖርተር) የአገሪቱን የዕድገትና ትራንስፌርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብለው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተመርጠው የገቡ ሦስት የውጭ ኩባንያዎች ላይ፣ ‹‹ጠላት ጥፋት ሊፈጽምባቸው እንደነበር ደርሰንበታል፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ባለፈው ቅዳሜ ታኅሣሥ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

‹‹ጠላት›› በተባለው አደጋ ሊደርስባቸው ነበር የተባሉት ሦስቱ የውጭ ኩባንያዎች የቱርኩ አይካ አዲስ፣ የሆላንዱ ሼር ኢትዮጵያና የቻይናው ሁንጂያን የጫማ አምራች ኩባንያዎች ናቸው፡፡ ‹‹የጠላት የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ነበር፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም ይህንን የጥቃት ጉዳይ ያነሱት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ለመብታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ኢንዱስትሪዎችንም ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት እንዳለባቸውና አንዳንድ ሠራተኞችም በእኩይ ተግባር ላይ ሊሰማሩ እንደሚችሉ በመጠቆም ነው፡፡

ጥቃት ሊፈጸምባቸው ነበር ስላሉዋቸው ኩባንያዎች ጉዳይ ሲገልጹም፣ ‹‹እነዚህ ሦስት ኩባንያዎችን በአንድ ሳምንት በተመሳሳይ ቀን የገጠማቸውን ልንገራችሁ፡፡ የዕድገታችን ጠላት ይህንን መንግሥት ማሽመድመድ የሚቻለው እነዚህን ሦስት ድርጅቶች በመምታት ነው ብሎ አቅዶ በድርጅቶቹ ውስጥ በመሠረተው ሴል አማካይነት ለአንድ ቀን እንዲጨናነቁ አድርጓል፤›› ብለዋል፡፡Israeli Newspaper Claimed Mandela received weapons training from Mossad agents in Ethiopia

1048642127

Top-secret archive document also reveals that Mandela was ‘familiar with the problems of Jewry and of Israel’ and that Israeli operatives tried to ‘make him a Zionist.’
Nelson Mandela, the former South African leader who died earlier this month, was trained in weaponry and sabotage by Mossad operatives in 1962, a few months before he was arrested in South Africa. During his training, Mandela expressed interest in the methods of the Haganah pre-state underground and was viewed by the Mossad as leaning toward communism.

These revelations are from a document in the Israel State Archives labeled “Top Secret.” The existence of the document is revealed here for the first time.

It also emerges that the Mossad operatives attempted to encourage Zionist sympathies in Mandela.

Mandela, the father of the new South Africa and a Nobel Peace Prize laureate, led the struggle against apartheid in his country from the 1950s. He was arrested, tried and released a number of times before going underground in the early 1960s. In January 1962, he secretly and illegally fled South Africa and visited various African countries, including Ethiopia, Algeria, Egypt and Ghana. His goal was to meet with the leaders of African countries and garner financial and military support for the armed wing of the underground African National Congress.