Category Archives: Interviews

ቴዲ አፍሮ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ያደረገው ቃለመጠይቅ

1479394_596908333697995_36575830_n

በሳምንቱ መጨረሻ ቴዲ አፍሮ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ነበረው፡፡ በሁለት ክፍል የተደረገውን ቃለ-ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል እነሆ ፡)

“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”

“ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣል”

“ፍቅር ያሸንፋል– የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው”

“እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው

“ከታሪክ ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”

የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡ መነሻው ምንድነው?

“አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤
የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣
ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣
አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…”

እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉበት – ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን

ዕንቁ መፅሔት ቆርጦ አስቀርቶታል የተባለው የቴዲ አፍሮ አስተያየት

enqu-magazines-cover-quoting-teddy-afro-as-saying-for-me-meniliks-unification-campaign-was-a-holy-war-ethiopia

(Daniel Berhane)

ዕንቁ፡- ዳግማዊ ምኒልክ ስለዛሬይቱ ኢትዮጵያ መፈጠር ሲሉ የገቡበትን ጦርነት እንዴት ነው የምትመለከተው?

ቴዎድሮስ፡- ምኒልክ በዚያን ጊዜ ያካሄዷቸው ፖለቲካዊ ተግባራት፣ በተለያዩ የአገሪቱ ግዛቶች በመዘዋወር ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ የገቡበት ጦርነት ለእኔ ቅዱስ ጦርነት ነው። ይህም የራሴ ዕምነት ነው። ምንጊዜም ሰዎች የሚበጃቸውን ነገር እስኪገነዘቡት ድረስ ያለመግባባቱ መጠን ይሰፋል። ያም ግጭት ሊፈጥር ይችላል። ወይም ደግሞ በእኛ ሀገር ሁኔታ ብቻ የተከሰተ ሳይሆን በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሆነም ነው። እንዲህም ሆኖ ግን ምኒልክ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ዘምተው ንጉሥ ጦናን ማርኩ። ከማረኳቸውም በኋላ እግራቸውን እያጠቡ ‹‹የእኛ አንድ አለመሆን፣ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት አለመመሥረታችን፤ የጋራ ለሚሆነው ጠላታችን ጥቃት አሳልፎ የሚሰጠን አደገኛ ሁኔታን የሚፈጥር ነው። በዚህ ምክንያት ነው ወደ አንተ ጦር ያዘመትኩት እንጂ ሥልጣንህን ለመቀማትና በአንተ ላይ ለመግነን… ፈልጌ አይደለም። ማእከላዊ መንግሥታችንን ማጠናከሩ ግን ሁላችንንም የሚጠቅመን ነው። አገራችንን፣ በሕላችንን፣ ታሪካችንን፣ ቋንቋችንን ጠብቀንና ድንበራችንን አስከብረን ለመኖር ይረዳናል›› ነበር ያሏቸው።

እንግዲህ ምኒልክ ንጉሥ ጦናን አሏቸው እንደሚባለውም ይሁን በሌሎችም ብሔራዊ ክብርንና ማንነትን አስጠብቆ ለመኖር በሚያስችለው ፖለቲካዊ መመዘኛ ሲታይ፤ ቋንቋንም ጠብቆ ለመኖር እንኳ ቢያስፈልግ… ከጠላት ማንኛውም ጥቃት ራስን መከላከል ወይም ማስከበር በሚቻልበት አቅም መጠን መኖርን የግድ ይላል። ምናልባትም በዚያን ጊዜ እንደ ምኒልክ ያለው ባለውለታ ተፈጥሮልን… ከጠላት ተጠብቀን መኖር ባንችል ኖሮ፤ ዛሬ የምንጠራበት ስማችን ኢትዮጵያዊ ቀለም ሊኖረው አይችልም ነበር። እኔም ቴዎድሮስ፣ ሌላውም ምኒልክ፣ ጥላሁን፣ ፀሐይ… አንባልም ነበር። የነበረው ቋንቋችን ሁሉ ይጠፋ ነበር። ግን ቋንቋንም፣ ባሕልንም ሰብስቦ ለመያዝ፤ ከዛም በላይ ደግሞ ሕዝብን አስተባብሮ በአንድነት ለመሥራት፤ የአንድነትን ታላቅ ዋጋ ቀድሞ መገንዘብ ያስፈልጋል። ያንን ቅዱስ ያልኩትን ጦርነት ሊያስነሳው የቻለውም ይኸው ግንዛቤ ይመስለኛል።

“ሁሉንም ትተነው ነው የምናልፈው፡፡ ሀብታችን ጌታ ብቻ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ

Hailemariam_Desalegn_Ethiopia

በጣም የሚወዱትን መዝሙር ይንገሩኝ?

አቶ ኃ/ማርያም፡- ‹‹እኔም እንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልልህ›› የሚለውን

ጉባዔ ገብተው ሲያመልኩ ግን እንደ ባለሥልጣን የፕሮቶኮል ነገር አለ፡፡ የጥበቃ ጉዳይ አለ፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ ይሄን ሁሉ ረስተው በነጻነት ለማምለክ አይቸገሩም?

አቶ ኃ/ማርያም፡ ምንም አልቸገርም፡፡ ጉባዔ ውስጥ ካለሁ እኔ ስለ ራሴ ጨርሶ አላስብም፡፡ እነ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ጨርቃቸውን ጥለው ያመልኩ ነበር፡፡ እኔስ የማመልከው እግዚአብሔር ፊት እንደሆንኩ እንጂ የማስበው ሌላ ነገር አላስብም ማልቀስ ካለብኝ አለቅሳለሁ፣ መንበርከክ ካለብኝ እንበረከካለሁ፡፡ ጌታ ሁን ያለኝን ሁሉ ለመሆን ዝግጁ ሆኜ ነው የማመልከው፡፡

ልጆችዎ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመክሊት (የአገልግሎት) ሥራ ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል፡፡ የእከሌ ልጅ ነኝ እኮ ብለው ሳይኩራሩ ወንድሞችና እህቶች የጠጡባቸውን የሻይ ብርጭቆዎች እየዞሩ ሲለቅሙ እንዳየ ወንድሜ ፍጹም ነግሮኛል፡፡ በቤት ውስጥ ምን ብለው ቢያስተምሯቸው ነው?

Interview with Bewketu Seyoum

ETHIOPIA---Seyoum,-Bewketu

SJF: Your work encompasses spoken word and performance, and comedy. Do you think this fluency of style is important in contemporary poetry?

BS: In Ethiopian tradition the spoken word has been much more respected than the written word. Till recently poets didn’t bother to put their verses on a paper. They would improvise in the presence of language- conscious audience who could in some extent participate in the composition. I believe some elements of this tradition is worth preserving.

“ውበትን ከማየት ይልቅ ለማሳየት እንባክናለን ” Teddy Afro’s New Interview with Addis Admas

teddy_afro

ስለ ኢትዮጵያ ማንነትና ታሪክ፤ ስለ አገራችን ባህልና አዝማሚያ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት፤ ከቴዲ አፍሮ ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ባለፈው ሳምንት ማቅረባችን ይታወሳል። በዛሬው የመጨረሻ ክፍል፤ በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ እናተኩራለን – የኪነጥበብ ፈጠራ ላይ። የመረጥነው ርእሰ ጉዳይ፤ በጣም አስፈላጊ የመሆኑን በዚያው ልክ ለውይይትና ለትንታኔ፤ ለጥያቄና ለመልስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ እንገነዘባለን። ቢሆንም ልንደፍረው ሞክረናል።

የኪነጥበብ የፈጠራ ስራ እንዴትና ከየት ይፈልቃል? የቴዲ አፍሮ ምላሽ፤ “ኪነጥበብ የሚፈልቀው ከስሌት ነው ወይስ ከስሜት?” የሚለውን ጥያቄ የሚያስቀይር ሊሆን ይችላል። ብቃትንና ሰብእናን፤ ነፍስንና ሃሳብን፤ ከራስ ጋር መሆንንና ውበትን፤ ፍቅርንና ቅንነትን እያወሳ ከኪነጥበብ ፈጠራ ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን እንደሆነ ቴዲ አፍሮ ሲናገር፤ ጥበብ አምልኮ ነው ይላል። ውበትን ማድነቅ አምልኮ ነው፤ ድንቅ ነገሮች ሁሉ የፈጣሪ ስራዎች ናቸውና በማለትም ይገልፃል።

Teshome Mitiku’s daughter Emilia Mitiku on BBC Breakfast

BBC Sports Interviews with Ethiopia’s Coach Sewnet Bishaw

coach_bishaw_sewnet-Ethiopia

Less than a week ago the Ethiopia coach Sewnet Bishaw could stroll the streets of Addis Ababa and nobody would have taken much notice.
Now the 59-year-old waves and embraces Ethiopian fans who greet him following his team’s 1-1 away in South Africa in their opening 2014 World Cup qualifier.
“The people are very happy – they like it very much when we win,” he said.
“For us the result against South Africa was more than a draw – it was a victory,” Bishaw told BBC Sport.

Activism and music in the life of a legendary singer

Ali BirraAli Birra is a man of great talent. For many Ethiopians the video that is shown on ETV was the closest presence they could ever get. Watching his songs on ETV, many people have sung along even if they do not understand the language. The saying “music is a universal language” seems to work perfectly in his case. He captivated many people who do not even speak Oromiffa.