Category Archives: Business

Nib bank grosses over 380 million birr profit

Nib bank

Finalizes plans to erect 33-storey HQs building

By Birhanu Fikade

Despite the National Bank of Ethiopia (NBE)’s T-bills directive, which requires private banks to invest 27 percent of their loan disbursement and is blamed for causing both liquidity and lending capacity shortages,

Nib International Bank (NIB) has managed to secure an all-time record of 389.5 million birr gross profit and netted 286 million birr after tax. The net profit grew by more than 40 million birr from the preceding fiscal year, the bank said.



ሼክ አል አሙዲ በኢትዮጲያ ትልቁን የብረታ ብረት ፋብሪካ ሊያስገነቡ ነው

sheik_mohammed

ሼክ መሐመድ አል አሙዲ በኢትዮጵያ ውስጥ መዋለ ነዋያቸውን ካፈሰሱባቸው ፕሮጀክቶች ትልቁ ያሉትን የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካ ገንብቶ ለማስረከብ ከመረጡት የጣሊያን ኩባንያ ጋር ለመፈራረም ባሰናዱት ዝግጅት ላይ፣ በቅርቡ የተሾሙትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ መንግሥት ለንግዱ ኅብረተሰብ ማድረግ የሚጠበቅበትንና የንግዱ ኅብረተሰብ ከመንግሥት የሚጠብቀው ነው ያሉትንም አዋዝተው ተናግረዋል፡፡

የጦሳ ብረታ ብረት ፋብሪካን ለመገንባት የጀርመን፣ የብራዚልና የቻይና ኩባንያዎች መወዳደራቸውን በንግግራቸው መጀመርያ ላይ የገለጹት ባለሀብቱ፣ የጣሊያኑ ኩባንያ በቻይና ዋጋ የአውሮፓ ቴክኖሎጂን ይዞ በመቅረቡ 13.7 ቢሊዮን ብር የሚፈጀውን ፋብሪካ ሙሉ ለሙሉ ገንብቶ ቁልፉን እንዲያስረክብ መምረጣቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

‹‹ወደ ፀጉር አስተካካይ ከመሄድህ በፊት መቀስ አያያዙን እየው፤›› የሚለውን የዓረቦች አባባል የጠቀሱት ሼክ አል አሙዲ፣ የጣሊያኑ ኩባንያን የመረጡበት ምክንያትም አያያዙ ስላማራቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ቀጠል አድርገው የተናገሩት ግን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን መሪነት ሥነ ሥርዓቱን ለመከታተል ለተገኙ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን የሚመለከት ይመስላል፡፡ ከባለሥልጣናቱ መካከል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦን፣ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ሚኒስትር አቶ መኩሪያ ኃይሌ፣ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጐበዜ፣ አቶ አዲሱ ለገሰ፣ አቶ ስብሐት ነጋና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡



ንግድ ባንክ ለሼክ አል አሙዲ ፈቅዶት የነበረው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር ታገደ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በቅርቡ ለሼክ መሐመድ አል አሙዲ የፈቀደው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲታገድ መወሰኑን የንግድ ባንክ ምንጮች ገለጹ፡፡ ንግድ ባንክ ይህን ብድር ለመስጠት ሲስማማ የማበደር አቅሙን አልፈተሸም፣ ዘንድሮ ከባንኩ ብድር የሚፈልጉ እንደ ስኳር ፕሮጀክቶች የመሳሰሉ የመንግሥት የልማት ዕቅዶች የብድር ፍላጎት በአግባቡ አልተጤነም፣ እንዲሁም በአንድ ጊዜ ለአንድ ተበዳሪ ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑ ስለታመነበት፣ ብድሩ ለጊዜው እንዲቆም መንግሥት መወሰኑን እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ተበዳሪው ሼክ አል አሙዲ ብድሩን ለመውሰድ ጥያቄ ያቀረቡት ለአፍሪካ ኅብረት ለሚያሠሩት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ሕንፃ ሊፍት መግዣና መግጠሚያ ነው፡፡ ብድሩም በቀጥታ ሊሰጥ የታቀደው ሊፍቱን ለሚያስመጣው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ለተባለው ሌላኛው የሼክ አል አሙዲ ኩባንያ ሲሆን፣ ንግድ ባንክ ለሊፍቱ ማስመጫ ራሱ ኤልሲ ከፍቶ ኮሚሽን ከማግኘት ይልቅ፣ በኤልሲ ኮሚሽን የሚያገኘውን ገቢ ትቶ በቀጥታ ለኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ብድሩን ለማስተላለፍ መምረጡ፣ የብድር ክፍል ሠራተኞችን ያስገረመ ጉዳይ እንደሆነ የባንኩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡



በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ 500 የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮች ተመረቱ

transformer

አዲስ አበባ ውስጥ ኮተቤ አካባቢ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው አድቫንቴጅ ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ከ500 በላይ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችን አምርቶ ለተጠቃሚዎች አቀረበ፡፡

ኩባንያው በአገር ውስጥ ያለውን የትራንስፎርመር ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ አርክቶ ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ የሚያስችለውንም እንቅስቃሴ በማከናወን ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ዳዊት ሐጎስና ሰይፈ ገብርኤል ሐጎስ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾች ሚስተር ስዊንድር ሲንግ ከተባሉ ህንዳዊ ጋር ተባብረው ያቋቋሙት ይኼ ኩባንያ፣ በዓመት እስከ 700 የሚጠጉ አዳዲስ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችን የማምረት አቅም እንዳለው ተናግሯል፡፡



Ethiopia has oil reserve larger than Kenya, Expects a discovery of oil within a year, Tullow Oil

safe_image

New drilling planned in Ethiopian concession

Tullow Oil Plc has signed an agreement with Ethiopian authorities to begin drilling operations in the South Omo Valley next January

Global oil and gas exploration company Tullow Oil Plc is to start drilling on the Ethiopian concession it has in South Omo Valley, Southern Regional State next January.



ለአፍሪካ የመጀመሪያው ድሪምላይነር አውሮፕላን በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባል

Ethiopian-Boeing-787-Dreamliner

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ካዘዛቸው አሥር ቦይንግ 787-8 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች መካከል የመጀመሪያው ነሐሴ 11 ቀን 2004 ዓ.ም. አዲስ አበባ ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አውፕላኑን ነሐሴ 8 ቀን በሲያትል ከተማ ዋሽንግተን ስቴት በሚገኘው የቦይንግ ፋብሪካ እንደሚረከብ አስታውቋል፡፡ አውሮፕላኑን ለመረከብ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማሪያም፣ ሌሎች ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ አዲሱ ለገሰና የትራንስፖርት ሚኒስትር አቶ ድሪባ ኩማ ወደ ሲያትል እንደሚያቀኑ ይጠበቃል፡፡

ነሐሴ 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ርክክብ ከተደረገ በኋላ በማግስቱ አውሮፕላኑ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይበራል ተብሏል፡፡ በአሜሪካዋ መዲና አውሮፕላኑ ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን የአሜሪካ ሴናተሮች፣ የተለያዩ አገሮች አምባሳደሮች፣ የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንዲጎበኙት ይደረጋል፡፡



ኢትዮ ቻናል ጋዜጣና ሳምሶን አድቨርቲይዚንግ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጉ

- አቶ ሳምሶን ማሞና ባለቤቱ ታስረው በ200 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀቁ

በሳምንት ሁለት ቀን (ረቡዕና ቅዳሜ) ለተወሰነ ጊዜ እየታተመ ከተሰራጨ በኋላ፣ በሕትመት ዋጋ መናር ምክንያት በሳምንት አንድ ጊዜ (ቅዳሜ) በመታተምና በመሰራጨት ላለፉት አምስት ዓመታት የቆየው ኢትዮ ቻናል ጋዜጣና ለ15 ዓመታት የማስታወቂያ ሥራ ሲሠራ የቆየው ሳምሶን አድቨርታይዚንግ፣ ከትናንት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ መወሰኑን ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሳምሶን ማሞ ለሪፖርተር ገለጸ፡፡ ድርጅቱን ለመዝጋት የወሰነበትን ምክንያት ተጠይቆ፣ የ2003 ዓ.ም. እና የ2004 ዓ.ም. የንግድ ፈቃድ አለመታደሱን ተከትሎ ‹‹ንግድ ፈቃድ ሳያድሱ በመሥራት ወንጀል›› ክስ ስለቀረበባቸውና የተጠቀሰባቸው የሕግ አንቀጽ እስከ 15 ዓመታት እንደሚያስቀጣ ስለተነገራቸው፣ ችግሩ መፍትሔ እስከሚያገኝ የወሰዱት ዕርምጃ መሆኑን ገልጿል፡፡



Investors Eying Full Auction of Ghion Hotel

Ghion-Hotel

The intended sale of Ghion Hotel Addis Abeba, known for its spacious 12ht compound and birdlife, has drawn a lot of attention from notable local and international investors.

Around 12 companies have so far bought bid documents including billionaire tycoon Mohammad Ali-Al Amoudi’s conglomerate MIDROC Ethiopia and importing giant GET-AS international, whose major owners are Getu Gelete and his brother Asrat; the tender will be opened on August 8.